Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 34 ኑ ሁላችን እንመልከት የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 34 ኑ ሁላችን እንመልከት የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ኑ ሁላችን እንመልከት
የጌታችንን ሥቃይ
ኃጢአትን ሊያስወግድ
ተሰቅሎ በመስቀል ላይ።
በየሱስ ክርስቶስ ሕመም
ተገኝቶልናል ሰላም።
፪፡ የየሱስ እጅና እግር
ተቸንክሮ ይታያል
የእሾህ ዘውድ ተደፍቶበት
ግንባሩን አቁስሎታል።
በየሱስ ክርስቶስ ሕማም
ተገኝቶልናል ሰላም።
፫፡ ነፍሴን በእጅህ ተቀበል
ሲል አባቱን ለመነ።
በመጨረሻም በመስቀል
ራሱን አዘነበለ።
በየሱስ ክርስቶስ ሕማም
ተገኝቶልናል ሰላም።
፬፡ ሰው ሆይ ስለ ኃጢአትህ
የሱስ ክርስቶስ ሞቶአል።
በደልህ እስከ መስቀል ሞት
መድኅኑን አድርሶታል።
በየሱስ ክርስቶስ ሕማም
ተገኝቶልናል ሰላም።

Exit mobile version