Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 339 ዘምር በፍቅር በደስታ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 339 ዘምር በፍቅር በደስታ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ዘምር በፍቅር በደስታ
የወንጌልን ቃል በሙሉ፥
የሱስ ይሰጣል ይቅርታ
ሕይወት ሰላምም ለሁሉ።
ዘምር፥ ዘምር ወንጌሉን
ከሁሉ ያ ሀብት ይደምቃል
ተካፈል በእልልታ አሁን
ያን ድንቅ የወንጌሉን ቃል።
፪፡ ዘምር የየሱስን ወንጌል፥
ፍርሃት ኀዘንም ይጠፋል።
ራሱን የሠዋ በመስቀል
ከሞት ሰውን ያድናል።
ዘምር . . .።
፫፡ ዘምር የየሱስን ጥሪ፥
አውጅ በዓለም ዙሪያ።
ዘምር ለጐበዝ ለፈሪ፥
መዳን ይገኛል ከዚያ።
ዘምር . . .።
፬፡ ዘምር የየሱስን ክብር፤
ከርሱ የሚበልጥ የለንም።
ዘምር የክርስቶስን ፍቅር፤
በሌላ ተስፋ አይገኝም።
ዘምር . . .።

Exit mobile version