Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 338 ወንድሜ ሆይ ቶሎ ና የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 338 ወንድሜ ሆይ ቶሎ ና የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡  ወንድሜ ሆይ ቶሎ ና።
ለምንስ ትዘገያለህ?
ጌታህም አንተን ይጠብቃል፤
ስፍራ ሊሰጥህ በርሱ ቤት፡፡
ለምን? ለምን?
ለምን ቶሎ አትመጣም
ለምን? ለምን?
        ለምን ቶሎ አትመጣም?
፪፡ ወንድሜ ሆይ ቶሎ ዳን፤
  በጌታ በየሱስ ጸጋ፡፡
  ያለርሱ መድኃኒት የለህም
  ፍፁሙም መንገድ እርሱ ነው፡፡
ለምን?. . .።
፫፡  ወንድሜ ሆይ አትቆይ፤
የርሱን ደኀንነት ተቀበል፡፡
ወደ ጌታህም እይ በእምነት፥
በደልህን ይቅር ይላል፡፡
ለምን?…፡፡
፬፡  ወንድሜ ሆይ አትቆይ፤
የመከሩ ጊዜ ያልፋል፡፡
ከመከራና ከድካምም
እርሱ ጌታ ያድንሃል፡፡
ለምን?…፡፡

Exit mobile version