Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 337 መከሩን ሁሉ የሚጠብቁ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 337 መከሩን ሁሉ የሚጠብቁ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ መከሩን ሁሉ የሚጠብቁ
ሰብሳቢዎች ወዴት ይገኛሉ?
ለጌታ ሥራ የሚሠሩ
በእውነት ለጌታ የሚገዙ?
ማን ይላካል? ማን ያገልግል?
የጌታን መልእክቱን
ማን ያዳርስለታል?
ስለ ሰማይ ማን ይጥራል?
የሕይወት አክሊል እንዲያገኝ።
፪፡ በከተማዎች በገጠሮችም
መልካም ሰብሉ ይገኛል በሁሉ።
ሰዓቱ ሳያልፍ ታጠቁ ንቁ፤
ነፍሳትን ሁሉ ለማዳን ትጉ።
ማን ይላካል . . .።
፫፡ የመከሩ ጊዜ ተዳርሶአል።
የጌታን ሰብል ሁሉ ሰብስቡ፤
ስለ ድካማችሁ ተደስቱ፤
የደስታን አክሊል ተጐናጸፉ።
ማን ይላካል . . .።

Exit mobile version