Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 334 ቅዱስ አምላክ ሆይ ባንተ ፊት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ቅዱስ አምላክ ሆይ ባንተ ፊት
ሕዝብህ የሚቀርብበት
ያ ብሩክ ቀንህ ይምጣለት።
አውርድለት በረከት፥
በዚያን ጊዜ ስብሐት
ይቀርባል ከአእላፋት።
፪፡ ምሥራቅ፥ ምዕራብ፥ ደቡብ፥ ሰሜን
ይድረስ የወንጌል ትምህርት።
በምድር ግርማህ ይገለጥ
ላንተ ይሁን ታላቅነት።
አብዛ ምእመናን
ስጣቸው ሰላም ደስታን።
፫፡ ትሰማለህ ስንለምንህ
ቢዘገይብን እንኳ፥
አሕዛብን ለማሳመን
ለፍቅርህ የለውም ወሰን።
ጸጋህን ለምታሳይ
ስብሐት ላንተ በሰማይ።