Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 330 እቀርባለሁ እቀርባለሁ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ እቀርባለሁ እቀርባለሁ
ጌታን ለማየት እሻለሁ።
ነፍሴ ጌታዋን ናፈቀች፥
መድኃኒትዋንም ፈለገች፥
እፊቱ እንድትቆም።
፪፡ ቅዱስ፤ ቅዱስ፤ ቅዱስ ጌታ
ብለው ሲዘምሩ ብፁዓን፥
ለመብረር ክንፍ ቢኖረኝ፥
በርሬ ቶሎ በሄድኩኝ፥
በዚያ ቤት ለመገኘት።
፫፡ ታላቅ ደስታ፤ ታላቅ ደስታ፥
በዚያ በታላቅ አዳራሽ።
ከቅዱሳን ጋር መኖር
ማንም በማይገምተው
በታላቁ ያምላክ ቤት።
፬፡ እርዳን ጌታ፤ እርዳን ጌታ
ወደ ሰማይ አድርሰን፤
ከሕይወት ምንጭ አጠጣነ።
አዲስ መዝሙር ለመዘመር
ጌታ የሱስ ሆይ አብቃን።
