Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 33 መስቀልህን ተሸክመህ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ መስቀልህን ተሸክመህ፥
ወደ ሞት ሄድህ ጌታ፤
ኃጢአተኞችን ለማዳን፥
ተሠዋህ በጎልጎታ።
ግሩም ፍቅርህ፥
ቅዱስ ደምህ፣
ለእኛ ነው የተሰጠ።
፪፡ የመስቀል ሸክም ከባድ ነው፥
ሲጨመር የኛ ዕዳ።
ጌታ ኢየሱስ እንዴት ቻልከው፥
መራራውን የሞት ጽዋ?
አሳስበን
ደንቅ ፍቅርህን፥
ነፍስን የሚያረካ።
፫፡ የመስቀልን ሞት መረጥህ፥
ያባትህን ዙፋን ትተህ፤
ፍቅርህን ልትገልጥልን፥
ስለኛ ተዋረድህ።
ይታገሣል፥
ያሸንፋል፥
ጌታ ሆይ፥ ያንተ ፍቅር።
፬፡ በመስቀልህ ሥቃይ ጌታ፥
ሞትን አሸነፍህልን።
ድልን ሰጥተኸን በደስታ፥
ወደ ሰማይ አድርሰን።
በሃይማኖት፥
የነፍስ ዕረፍት
በዚያ እናግኛለን።
