Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 329 ወዳንተ የሱስ ሆይ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 329 ወዳንተ የሱስ ሆይ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ወዳንተ የሱስ ሆይ
ልቤ ይናፍቃል፥
የአምላክ በግ ሁነህ
ስለኔ ሙተሃል።
፪፡ ሰላም ለኔ ሰጠህ
ተሸክመህ ቅጣት
ታዳጊዬም ሁነህ
አወጣኸኝ ከሞት።
፫፡ ለኔም ባባቴ ቤት
ስፍራ አዘጋጀህ፤
ዓይናችን ያላየው
ብርሃኑም አንተ ነህ።
፬፡ ከዓለም መሄዴ
በደረሰ ጊዜ፤
ምራኝ በብርሃንህ
ልገባ አገሬ።

Exit mobile version