Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 323 ከከንቱ ዓለም የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ከከንቱ ዓለም
ስጓዝ ወደ ሰማይ፥
ቶሎ ደከምኩኝ፤
የሱስ ግን ደገፈኝ።
በእጁም ያዘኝ፤
በፍቅሩ ረዳኝ፤
በፍቅሩ ረዳኝ።
፪፡ ስራመድ ሳለሁ
ወደ ላይኛው ቤት፥
በላዬ ያለውን
የኃጢአት ሸክሜን
አይቶ ችግሬን
አወረደልኝ፤
አወረደልኝ።
፫፡ ከባድ ሸክሜን
አነሣልኝ በጁ፤
ዕረፍትም ሰጠኝ፤
አቀፈኝ በክንዱ።
እየመራኝም፥
ቤቱ አስገባኝ፤
ቤቱ አስገባኝ።
፬፡ የዓለም መድኅን
ስለኛ የሞትህ፥
ሕይወት የሆንህ
በኃጢአት ለሞቱ፥
ለእኔ ደግሞ፥
ሕይወትን ሰጠኝ፤
ሕይወትን ሰጠኝ።
