Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 319 ወደ ከበረው አገር በላይ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 319 ወደ ከበረው አገር በላይ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ወደ ከበረው አገር በላይ
እናያለን በሃይማኖት ዓይን፤
ጥሩ ቤት አለን በሰማይ
የተዘጋጀ በየሱስ ሞት።
ቅርብ ነው ጊዜው
ልንገናኝ በሰማይ አገር፥
ቅርብ ነው ጊዜው
ልንገናኝ በሰማይ አገር።
፪፡ ስንፈታ ከሞት እሥራት፥
እንኖራለን በዚያ ድንቅ አገር።
ከጌታችንም ጋር በአርያም
ልንዘምር ነው የብፁዓን መዝሙር።
ቅርብ ነው . . .።
፫፡ አምላካችን የፍቅር አባት፥
ስለ ገለጥህልን ፍቅርህን፥
ስለ ሰጠኸንም ጸጋህን
እናመስግንህ እለት እለት።
ቅርብ ነው . . .።

Exit mobile version