Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 310 እንሰብሰብ በዔደን አንድ ቀን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ እንሰብሰብ በዔድን አንድ ቀን፥
ከዚህ ምድር ሥቃይ እንዳን።
የዘንባባ ዝንጣፊዎች ይዘን፥
እንቅረብ ወደ አምላክ ዙፋን።
ወደ ላይ ስንደርስ፥
ወደ ላይ ስንደርስ።
የዘላለም ብፅዕና ይሆነናል፤
ወደ ዔድን አንድ ቀን ስንደርስ።
፪፡ ስንደርስ ወደ ዔድን አንድ ቀን፥
ጻድቃን ሁሉ ይቀበሉናል።
የሰማዕታት ጭፍራም ደስታችንን
ከእኛ ጋር ይካፈለዋል።
ወደ ላይ . . .።
፫፡ የሱስም ወዲያ አድርሶን
እርሱ ራሱ ይቀበለናል።
የሙሽራም ልባሳችንን አልብሶ
ከርሱ ጋር ያስቀምጠናል።
ወደ ላይ . . .።
