Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 31 የሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 31 የሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ
መከራ ተቀበለ።
እንደ ክፉ በደለኛ፤
በእንጨት ላይ ተሰቀለ።
እርሱ ቤዛ ሆኖአል፥
በኛ ፈንታ ሞቶአል።
፪፡ በሕማሙና በሞቱ፥
ምሕረት ተሰጥቶናል።
በትንሣኤው፥ በሕይወቱ፥
ለኛ ጽድቅ ተገኝቶአል።
በዕርገቱም ወደ ላይ
ስፍራ ሰጠነ በሰማይ።
፫፡ ምስጉን እርሱን የሚያምን፥
የሚቀበል ጸጋውን።
ተስፋው ከቶ አይናወጥም
በኃጢአት ቢጨነቅም።
ወደ ዘላለም ሕይወት
ይገባል በሃይማኖት።

Exit mobile version