Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 308 ጨለማው ሌሊት አለፈልን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 308 ጨለማው ሌሊት አለፈልን የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ጨለማው ሌሊት አለፈልን፤
የንጋትም ኮከብ ወጣልን።
የብፀዕና ቀን ደረሰልን
በአምላካችንም ምሕረት።
ክርስቶስ ይመጣል፥
ክርስቶስ ይመጣል፥
ሥቃይና ጭንቀት ሁሉ ያልፋል።
ደስታ ዕልልታም
ክብርም ይሆናል
ደስታችን ለዘላለም ነው።
፪፡ ከመከራና ከጭንቀት ሁሉ፥
ከችግርና ከፈትና፥
ከዚህም ሁሉ እንድናለን፤
የድል መዝሙር እንዘምራለን።
ክርስቶስ ይመጣል . . .።
፫፡ ቸሩ የዋህ ጌታ አነቃቃን
እንድንገናኝህ ሁልጊዜ።
ሰማይና ምድር ሁሉ ሲያልፍ፥
የሰጠኸን ተስፋ ይጸናል።
ክርስቶስ ይመጣል . . .።

Exit mobile version