Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 304 የአምላክ ጸጋ ምስጢር ነው የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የአምላክ ጸጋ ምስጢር ነው
የገለጠ ለኔ፥
የየሱስ ክርስቶስን ፍቅር
ለርሱ የዋጀኝን።
ግን አውቃለሁ የአመንኩትን፥
ተረድቻለሁ ችሎት እንዳለው፥
ከኃጢአት እንዲጠብቀኝ፥
እስከሚመጣበት ቀን።
፪፡ ጌታ እንዴት እንደ ሰጠኝ
አዳኙን ሃይማኖት፥
እንዴትም እንዳጸደቀኝ
ልረዳው ባልችልም።
ግን አውቃለሁ. . .።
፫፡ አላውቅም መንፈሱ እንዴት
በሰው እንዲሠራ
እየገለጠ የሱስን
እየሰጠ እምነትን።
ግን አውቃለሁ. . .።
፬፡ የጌታን መምጫ አላውቅም
ጥዋት ቢሆንም ማታም፤
እንዴት እንድሄድ አላውቅም
በግር ቢሆን ባየር።
ግን አውቃለሁ. . .።