Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 303 ብቸገር ብጨነቅም በኑሮዬ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 303 ብቸገር ብጨነቅም በኑሮዬ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ብቸገር ብጨነቅም በኑሮዬ፥
ከመድኃኒቴ አልለይም።
መላ ችግሬን ያውቃል መድኃኒቴ፤
ከእርሱ የሚሰወር የለም፤
ዝቅታ፥ ከፍታ አይጋርደውም።
፪፡ እግዚአብሔር በኃጢአቴ ብዛት
ለዘላለም አልተወኝም።
በጭንቀቴም የልብ ተስፋ እንዳልቆርጥ፥
መንፈሱን ሰጥቶኛል በዓለም፥
እርሱ ያስብልኛል ፍጹም።
፫፡ እርሱ የምመካበት ሕይወቴ ነው፤
ንፍሴን ከጥፋት ይጠብቃል፤
ቃሉንም ፈጽሜ እንድቀበለው፥
ታላቅ እምነትን ይሰጠኛል፤
በታላቅ ኃይሉም ይረዳኛል።

Exit mobile version