Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 3 ዮሐንስ በእስር ቤት ሆኖ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ዮሐንስ በእስር ቤት ሆኖ
ቢናፍቅ የሱስን፥
ቶሎ ላካቸው አፋጥኖ
ደቀ መዛምርቱን።
የናፍቆቱንም መልእክት የርሱ
እንደዚህ የሚል ነው፤
ትመጣለህ ብለን እኛ
የምንጠብቀው።
፪፡ ከቶ አንተ ትሆን ይሆን
ወይንስ ሌላ ነው ወይ?
ጌታም ላከው ይህን ቃል
እንዳይጠራጠር።
እውሮችም ነፃ ወጡ
ከጨለማ ቀንበር፤
አንካሶችም ቆመው ሄዱ
እፈቀዱት አገር።
፫፡ ለምጻሞችም ቶሎ ነጹ
ከርኵሰታቸው ነውር፤
ሙታንም ደግሞ ተነሡ
ከወኅኒ መቃብር።
ለችግሮኞችም ሁሉ፥
ወንጌል ይሰበካል፤
ምስጉን ነው ያ ሰው በእኔ
የማይሰናከል።
