Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 299 ስንጓዝ ሳለህ በጠባቡ መንገድ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 299 ስንጓዝ ሳለህ በጠባቡ መንገድ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ስትጓዝ ሳለህ በጠባቡ መንገድ
የኃጢአት ሸክም ይከብድብሃል ወይ?
ለየሱስ ስጠው ሁሉን ተናዘዝ፥
በጠባቡ መንገድ ይባርክሃል።
በጠባቡ መንገድ ከየሱስ ጋር ሂድ፤
ኃጢአትህን ሁሉ ይሸክማል፤
ኀዘንህን ሁሉ ይካፈልሃል፥
ጭንቀትህን ሁሉ ያርቅልሃል።
፪፡ ስትፈተን ሳለህ ተስፋ ስትቆርጥ
የሱስ ይረዳሃል ያበረታሃል፤
የልብህን ጥማት የሱስ ያረካል፥
ከሕይወት ምንጭ ውኃ የሱስ ያጠጣሃል።
በጠባቡ መንገድ . . .።

Exit mobile version