Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 297 አልጨነቅም ለመከራ የዘፈን ግጥሞች
አልጨነቅም ለመከራ
አምላክ ካለ ከእኔ ጋራ
አልጨነቅም ለመከራ
አምላክ ካለ ከእኔ ጋራ
፩፡ በሰጠኝ ተስፋ እጸናለሁ
በኢየሱስ ስም አምኛለሁ።
ከብስጭት እንድትድኑ
ሁላችሁም በእርሱ እመኑ።
ከብስጭት እንድትድኑ
ሁላችሁም በእርሱ እመኑ።
አልጨነቅም . . .።
፪፡ አትጨነቁ ለዚህ ዓለም
ከኢየሱስ የሚበልጥ የለም።
እናቶቼ አባቶቼ
አትታለሉ ዘመዶቼ
እህቶቼ ወንድሞቼ
አትዘንጉ ወገኖቼ።
አልጨነቅም . . .።
፫፡ ዓለም ያልፋል ሀብትም ሁሉ
የሚወዱን ይለያሉ።
ሞት ቢመጣ ጣር ሲከበን
ያኔ የለም የሚያድነን።
ሞት ቢመጣ ጣር ሲከበን
ያኔ የለም የሚያድነን።
አልጨነቅም . . .።
፬፡ ያታለሉን ነገሮች ሁሉ
ከፊታችን ይሸሻሉ።
የማይለይ የማይጠፋ
ኢየሱስ ነው ቋሚ ተስፋ።
የማይለይ የማይጠፋ
ኢየሱስ ነው ቋሚ ተስፋ።
አልጨነቅም . . .።
፭፡ ሁላችሁም ብልህ ሁኑ
በየሱስ አሁን እመኑ።
ተናዘዙ ለፈጣሪ
እርኅሩህ ነው ቸር መሐሪ።
ተናዘዙ ለፈጣሪ
እርኅሩህ ነው ቸር መሐሪ።
አልጨነቅም . . .።
