Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 296 ደስ ይበለኝ ኀዘን ይራቅልኝ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ደስ ይበለኝ ኀዘን ይራቅልኝ፤
እግዚአብሔር ይወደኛል።
አምላካችን አባት ከሆነልኝ፤
ስለ ልጁ እርሱ ያስባል።
በየደቂቃው የደረሰኝን፥
አባቴ በፍቅሩ ልኮታል።
ለየቀኑም የሚጠቅመኝን
ደስታም፥ ኃዘንም ያካፍላል።
፪፡ ጩኸቴን ለመስማት አይሰለችም፤
ሸክሜንም ያነሣልኛል።
በድካሜ ከኔ ዘንድ አይለይም
ስሙም መካር ኃያል ይባላል።
ክቡር ገንዘቡ እንዳይጠፋበት፥
እርሱ ራሱ ይጠነቀቃል፤
እንደ ቀኑም ኃይሉ ሊሆንለት
ልጁን ጸጋው ያበረታዋል።
፫፡ አምላኬ እንዲህ ስታስብልኝ፥
እኔም ሐሳቤን ልተው እርዳኝ።
እምነቴን ከቃልህ ጨምርልኝ
በዚህም ወዳገሬ ምራኝ።
ደስ ሲለኝ ስጨነቅም በኀዘን፥
አንተ ሁሉን እንደ ሰጠኸኝ፥
ተስፋህን ተቀብዬ ለማመን
ጌታ ሆይ አንተ አስተምረኝ።
