Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 294 ያች ታናሽ መንጋ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 294 ያች ታናሽ መንጋ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ያች ታናሽ መንጋ
ብፅእት ናት፤
የክርስቶስ ቤተ ሰው።
ጠላትም ቢያስጨንቃት፥
እረኛው ታላቅ ነው።
ከመከራ ያድናታል፤
በቃሉም ያበረታታል፤
በክንዱ ይሸከማታል፤
ቤቱም ያደርሳታል።
፪፡ በጎቹንም ያውቃቸዋል፤
እነርሱም ያውቁታል።
ልባቸው አዲስ ሆኖአል፤
ቃሉንም ያምኑታል።
በመንፈስ ኃይልና ብርሃን፥
ከፍርድ ከሰይጣንም ሥልጣን
ተቀበሉ ሙሉ መዳን
የአምላክ ቅዱሳን።
፫፡ አቤቱ ልቤን መርምረው
ላንተ ይቻልሃል።
በፍጹም ያንተ አድርገው
ስለርሱ ሙተሃል።
ችሮታህም ሳይታወቀኝ
በሕይወትህ የገዛኸኝ፥
እሞት ድረስ ከወደድኸኝ
ልወድህ አስተምረኝ።
፬፡ እኔን ትወደኛለህ ወይ?
ብለህ አትጠይቀኝ፥
እላለሁ ቸር አምላኬ ሆይ፥
አንተ ታውቃለህ ሁሉን።
ድካም ቢያጒላላኝም፥
በኃጢአት ብጨነቅም፥
ልከተልህ ልወድህም
ፈቃዴ ሆኖአል።
፭፡ ስቸር ስፈራ ምላሼን
መስጠት ቢቸግረኝ፥
አንተም ትላለህ ገንዘቤን
መውደድ አይገደኝም።
በሞት በሕይወት ወደድኸኝ፤
ለአንተም በደም ዋጀኸኝ፤
ቸር ወዳጄ ሆይ ላንተ ነኝ፤
በፊት ለወደድኸኝ።

Exit mobile version