Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 288 ኀዘንተኛን የሚያጽናናው የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 288 ኀዘንተኛን የሚያጽናናው የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ኀዘንተኛን የሚያጽናናው
የመድኃኒታችን ስም፥
ያን ቅዱስ ስም የሚጠራው
ይረዳል፥ ይድናልም።
ቅዱስ ስም፥ ብፁዕ ስም፥
የዘላለም ተስፋ ነው።
፪፡ ብርቱ ጋሻም ይሁንለት
ኃጢአት ሊፈትነው፤
ልመናውም ይፈጸምለት
ከየሱስ የለመነው።
ቅዱስ ስም . . .።
፫፡ ያ ክቡር የየሱስ ስምም
ብፅዕናን ይሰጠናል
ሕይወት ደስታም ሰላምም
ከዚህ ስም አግኝተናል።
ቅዱስ ስም . . .።
፬፡ ወደ ሰማያዊ አገር
አድኖ ሲያደርሰን፥
ያን ቅዱስ ስም ላምላክ ክብር
እንዘምር ደስ ብሎን።
ቅዱስ ስም . . .።

Exit mobile version