Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 284 በብዙ ትዕግሥትና ኀዘን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ በብዙ ትዕግሥትና ኀዘን
በተጠራንበት እንጽና፡፡
እንኑር ጌታችንን በማመን
እንድናገኝ ከርሱ ብፅዕና፡፡
ለብሰን የሃይማኖት ዕቃ— ጦር
ፍጹም እውነትን እንከተል
እግዚአብሔር ሊያኖረን በክብር
አዳኝ ልጁን ሰጥቶናል፡፡
፪፡ በቅድስና እንመላለስ
ያለምንም ተንኰልና ቂም
እኛ የእግዚአብሔር መቅደስ
ሆነናል በየሱስ ክርስቶስ ደም፡፡
የእርሱ ማደሪያዎች ከሆንን
መጥፎ ሥራችንን እንተው፡፡
አንድነታችንንም አጽንተን
እርሱን እንከተለው፡፡
፫፡ እግዚአብሔር የሚወደውን
እናድርግ ደስ እንዲለው በኛ።
የሠራልን የደሕንነት ኪዳን
ተፈጽሞልናል በጌታ።
እንግዲህ ጥፋት አይደርስብንም።
ከገሃነም ፍርድ አምልጠናል።
በኃጢአት ምክንያት አንጣልም
በጸጋው አድኖናል።
