Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 274 በእምነት ነው የዳነው የዘፈን ግጥሞች
፩፡ በእምነት ነው የዳነው
አዎ በእምነት ብቻ።
ክርስቶስ ባደረገልን
በራሱ ደምም በዋጀን።
አዎ በእምነት ብቻ
አዎ በእምነት ብቻ።
፪፡ በእምነት ነው የዳነው
በምግባራችን አይደለም።
ክርስቶስ ነው ያዳነነ
የራሱን ጽድቅ የሰጠነ።
አዎ በእምነት . . .።
፫፡ በእምነት ነው የዳነው
ጸጋውን በመቀበል
ወደ መስቀሉ በማየት
እኛ የተዋጀንበት።
አዎ በእምነት . . .።
፬፡ በእምነት ነው የዳነው
ሰማይ የኛ የሆነው
ከቅዱሳን ጋራ ሁነን
ሰማይ ቤት እንገባለን።
አዎ በእምነት . . .።
