Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 273 እኔ የሱስን ለማየት የዘፈን ግጥሞች
፩፡ እኔ የሱስን ለማየት፥
ከቶ አልተቻለኝም፤
ወይ ድካም የልቤ ዕውረት፥
እርሱን አያሳየኝም።
የሱስ ና ልቤን አብራልኝ።
ዓይኖቼን ክፈትልኝ።
ቀና መንገድህን አሳየኝ፤
ከጥፋትም አድነኝ።
፪፡ በባርነት የተጋዙ፥
አርነት ወጥተዋል።
ቦሪት መርገም ለተያዙ፥
ቡራኬ ተሰጥቶአል።
የክርስቶስ ደም ለነፍሳቸው፥
ሕይወት ሆነ ፈውስም።
የሱስ ክርስቶስ ሞተላቸው።
እርሱ ነው መድኃኒትም።
፫፡ ማን ነው ዛሬ የሚጠራ?
ፍቅሩን የሚገልጥ ማን ነው?
ለሚምትስ የሚራራ?
የሚያድንስ ማነው?
የሱስ ነው መድኃኒታችን፤
ስለ እኛ ሞቶአል።
ቅዱስ ስሙን የሚያምን፥
ለዘላለም ይድናል።
