Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 27 ስብሐት ለእግዚአብሔር የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ስብሐት ለእግዚአብሔር
ስብሐት ለአንድ ልጁ
ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ስም
ካሁን እስከ ዘላለም።
ሳናውቀው አወቀነ
ሳንወደው ወደደነ።
ሳንሻው ፈለገነ
ልጆቹ ልንሆን።
፪፡ ርኅሩኅ አባት ከሰማይ
አየን አሽቆልቁሎ
በዓለም እድፍም ተውጠን
ጠፍተንም ተባርረን።
ኃጢአታችን ሸፍኖን
ርኩሰትም አሸንፎን
ወገኖቹም ተጨንቀው
መድኃኒት አጥተው።
፫፡ ተስፋ ተሰጥቶን ነበር
ያም ተስፋ ቃል ነበር።
ነቢያት ያስጠነቀቁት
የመምጣቱን ነገር
በሰው ፈቃድም ሳይሆን
ግን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል
ሰው ሆነ ሥጋ ለብሶ
ባለም ተገለጠ።
