Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 269 በጽዮን ደንጊያ አኖረ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ በጽዮን ደንጊያ አኖረ
ልዑል እግዚአብሔር
በእርሱ ዘንድ የከበረ
የተናቀ በምድር።
፪፡ የማእዘኑም ራስ የሱስ ነው
የሚያምንበት
ከቶ አያፍርም አይወድቅም
ግን ያገኛል ሕይወት።
፫፡ ጌታችን የሱስ ክርስቶስ ነው
ይህም የማዕዘን ራስ
ጽኑ መሠረት እርሱ ነው
ዘላለም የማይፈርስ።
፬፡ ያለርሱ መሠረት የለም
ሰው የሚጸናበት
በራሱ ኃይል ብቻ ቢቆም
ይሆንበታል ውድቀት።
፭፡ በዚህ መሠረት የሠራ
እርሱ ነው ጠቢብ ሰው
የለውም የሚያስፈራ
እስከ ፍጻሜው።
፮፡ ልባችን መቅደስ እንዲሆን
ለልዑል እግዚአብሔር
ስለዚህ ቅዱስ መንፈሱን
አወረደው ለሰው።
