Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 265 ጌታ ሆይ ደምፅህን አሰማለሁ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ጌታ ሆይ ደምፅህን አሰማለሁ
ፍቅርህ የሚነግረኝን፥
እጄን ወዳንተ እዘረጋለሁ፥
ወዳንተም አቀርባለሁ።
የሱስ ወደ አንተ አቅርበኝ
ወደ ልብህ ጌታ ሆይ።
ወደ አንተ ጌታ የሱስ አቅርበኝ
ወደ መስቀለህ ሥቃይ።
፪፡ ባምላካዊ ኃይል አበርታኝ አሁን
አንተን እንዳገለግል
ባንተ ጸጋና ባንተ ቸርነት
ለዘላለም ጠብቀኝ።
የሱስ ወደ አንተ . . .።
፫፡ ጌታ የሱስ ሆይ በዙፋንህ ፊት
ለጸሎት ስንረከክ
ቸሩ ወዳጄና መድኃኒቴ
ጸሎቴን አድምፅልኝ።
የሱስ ወደ አንተ . . .።
፬፡ ያምላክ ፍቅር ምንጭ
ምንኛ ጥልቅ ነው
የሚገኘው በጸጋው
በመጨረሻም አገኘዋለሁ
በሰላም ከደረስሁ።
የሱስ ወደ አንተ . . .።
፭፡ የሞትንም ባሕር ተሻግሬ
ፍቅርህ ግልጥ ሲሆን ለኔ
አዲስ መዝሙርን እዘምራለሁ
ምስጋናም አቀርባለሁ።
የሱስ ወደ አንተ . . .።
