Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 264 ለምን አትነሣም ወንድሜ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ለምን አትነሣም ወንድሜ
እንዳያልፍብህ ጊዜው።
መድኃኒታችን ይጠራሃል
ሰላሙን ሊሰጥህ ነው።
ዛሬ ዛሬ የደኅንነት ቀን ነው
አሁን አሁን አሁን የጸጋ ጊዜ ነው።
፪፡ ለምን አትነሣም ወንድሜ
የምሕረት ጊዜ ቀርቦአል።
ለጌታ ብቻ ስገድለት
ሰይጣንን አትከተለው።
ዛሬ ዛሬ . . .።
፫፡ የአንተ ኃጢአት ይቅርታ
በቅዱስ ደሙ ብቻ ነው።
የዘለዓለም ብፅዕናን የሚሰጥህ
ጌታ ብቻ ነው።
ዛሬ ዛሬ . . .።
፬፡ አሁንም ንቃ ወንድሜ ሆይ
የምሕረት ጊዜ ሳለህ።
በሩ ተከፍቶልሃልና ሳይዘጋብህ
ቶሎ ና።
ዛሬ ዛሬ . . .።
