Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 263 ኃጢአትህን ለተሸከመው የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ኃጢአትህን ለተሸከመው
ለኢየሱስ ስፍራ አለህ ወይ?
የልብህን በር ቢያንኳኳ
አትከፍትለትም ወይ?
የሱስን ታላቁን ንጉሥ
አሁን ፈጥነህ ታዘዘው።
የልብህን በር ክፈተው
አሁን እርሱን አስገባው።
፪፡ ላለም ለደስታ የሚሆን
በልብህ ውስጥ ስፍራ ሲኖር።
ለኢየሱስ ለሞተልህ ግን
ስፍራ አጣህለት ወይ
የሱስን . . .።
፫፡ በፍቅር ለሚለምንህ
ለኢየሱስ ስፍራ አለህ ወይ
ስለ ነገ አታውቅም
የመዳን ቀን ዛሬ ነው።
የሱስን . . .።
፬፡ ልብህን በሙሉ ስጠው
የጸጋ ቀን ሳያልቅብህ።
የምሕረት ቀን ሳያልፍብህ
ልብህን ክፈትለት።
የሱስን . . .።
