Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 262 ደካሞች የሱስ ሲጠራችሁ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 262 ደካሞች የሱስ ሲጠራችሁ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ደካሞች የሱስ ሲጠራችሁ ስሙ።
ሸክማችሁም የከበደ ሁሉ፥
ኑ ለዘላለም ዕረፍትን ልስጣችሁ፥
ችግራችሁንም ላቃልላችሁ፥
ኑ ወደኔ ከእኔ ተማሩ፥
ቀንበሬ ልዝብ ነው
ሸክሜም ቀሊል ነው።
የዋህ ነኝ፥ ትሑት ነኝ
በእኔ እመኑ፥
ኑ ላሳርፋችሁ፥ ኑ ልባርካችሁ።
፪፡ በኀዘን የተጨነቃችሁ ሁሉ፥
ጥርጥርና ሐሳብ ያጠቃችሁ፥
ችግራችሁን ለየሱስ ንገሩ፥
ጭንቃችሁንም ለርሱ አስረክቡ።
ኑ ወደኔ . . .።
፫፡ ፈተና ማሸነፍ የተሳናችሁ፥
ሕይወታችሁ የተዳከመባችሁ፥
ኑ ወደ የሱስ፥ ኃይል እንድታገኙ፥
በመንፈስ ቅዱስ እንድትታደሱ።
ኑ ወደኔ . . .።

Exit mobile version