Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 260 የምስራች ሰምተህ እመን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 260 የምስራች ሰምተህ እመን የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የምሥራቹን ሰምተህ እመን፥
የሱስ ፈጽሞ አዳነን።
ሰውን ሊያድን በምሕረት
ነው የጥንቱ የአብ ሥምረት።
ወልድም ዋጀልን ሰርየት።
፪፡ የምስራቹን ሰምተህ እመን፥
የሱስ ፈጽሞ አዳነን።
ብቻውን ሆኖ ድል ነሥቶአል፤
የእባብን ራስ ረግጦአል፤
ሰማይን ከፍቶልናል።
፫፡ የምስራቹን ሰምተህ እመን፥
የሱስ ፈጽሞ አዳነን።
ባንተ ውስጥ የሚነቀፈውን፥
ሕግ ሊሠራ የማይችለውን፥
የሱስ ፈጽሞልሃል።
፬፡ የምሥራቹን ሰምተህ እመን፥
የሱስ ፈጽሞ አዳነን።
ኃጢአትህ ከብዶብሃል፥
መርገምም ተጭኖብሃል፥
የሱስ አድኖሃል።
፭፡ የምሥራቹን ሰምተህ እመን፥
የሱስ ፈጽሞ አዳነን።
ርኩስ ኃጠአተኛ ነህ፤
የሱስ ግን ስለ ወደደህ፥
ካምላክ ጋር አስታረቀህ።
፮፡ ተቀብለህ ደስ ይበልህ፥
የሱስ ሁሉ ሲሆንልህ።
የሚያስፈልግህን ሁሉ፥
ከመድኃኒትህ ካገኘህ፤
ጻድቅም፥ ቅዱስም ነህ።
፯፡ ተቀብለህ ደስ ይበልህ፥
የሱስ ሁሉ ሲሆንልህ
ስትጨነቅ ይረዳሃል፥
ባይታይልህም ቀርቦልሃል፤
በጁም ይደግፍሃል።
፰፡ ተቀብለህ ደስ ይበልህ፥
የሱስ ሁሉ ሲሆንልህ
ካለም መከራና ድካም
መድኃኒትህ ያሳርፍሃል
በዘለዓለም ሰላም።

Exit mobile version