Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 26 የገና ቀን ደስታችን ነው የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 26 የገና ቀን ደስታችን ነው የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የገና ቀን ደስታችን ነው
የሱስ የመጣለት
መላእክት ሌሊት ዘመሩ
ኮከቡን አበራልን።
፪፡ የቤተልሔም ታናሽ ሕፃን
ግሩም ንጉሥ ሆኖአል
የሰማይ ደስታ ሊሰጠን
ወደኛ ወርዶአል።
፫፡ አሁን በሰማይ በአብ ቤት
በክብር ይኖራል
ግን ጸሎታችንን በሌት
በቀንም ይሰማል።
፬፡ በገና ቀን ደስ ይለናል
ከፍ ባለ ምስጋና
ሕፃኑም ደስታን ይሰጠናል
ለርሱ ሃሌ ሉያ።
፭፡ የሱስ የመጣ ዕለት ማታ
ታላቅ ብርሃን ታየ፤
እረኞችም በችኰላ
መጡ ወደ ጌታ።
፮፡ ያ ኮከብ ያበራል ገና
ብናምን ያምላክን ቃ
ይሰጣል የሰማይ ደስታ
ለሕይወት ይመራል።
፯፡ የሰማይ ሰራዊት ሁሉ
በደስታ ዘመሩ
ሰላም ለዓለም በሙሉ
ይሁን እያሉ።
፰፡ ኦ ኢየሱስ እኔን እርዳኝ
ላንተ እንድዘምር
በእጅህም እኔን ምራኝ
ልኑር ላንተ ክብር።

Exit mobile version