Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 252 የልብህን በር የሚመታ ማን ነው? የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የልብህን በር የሚመታ ማን ነው?
ማን ይጠራል?
በደሙ የገዛህ መድኃኒትህ ነው!
በፍቅሩ ለአንተ ይራራል።
፪፡ ከጥንቱ ሲጠራህ ሲፈልግህም፥
ሰምተሃል ወይ?
ለጌታ ለርኅሩኅ መድኃኒትህም
የልብህን በር ከፍተሃል ወይ?
፫፡ የዓለም ከንቱነት የልብህን
ጥም አያረካም።
ወዳለምም ደስታ ፈቃድህ ሲሳብ
መባባት ከልብህ አይጠፋም።
፬፡ የዓለምን ሁሉ ክብርና
ጥሪት ብትወርስም፥
ከምድር ብቻ የምታገኘው ሀብት
ሰላምን ሊሰጥህ አይችልም።
፭፡ በሰው ወዳጅነት በዓለምም
ሸር ብትመራ፥
ረድኤት ስትሻ ሳታገኝ ብትቀር
ያጋልጡሃል ስትጠራ።
፮፡ ግን ኢየሱስ ቢሰጥህ የእውነት
ሰላም ለዘላለም።
ከእርሱ በቀር ሌላ ሀብት አትሻም፥
አይተውህምም በዚህ ዓለም።
፯፡ የየሱስ ወዳጅ ከመሆን
የሚበልጥ ምን ይገኛል?
የፍቅሩን የጸጋውንም መብለጥ ሲገልጥ
ከእርሱ በቀር ምን ያስመኛል?
፰፡ ብፅዕና ሊሰጥህ ለመጣው
ወዳጅ ክፈትለት፤
ለአንተም ብጽዕና ሲያዘጋጅ፥
የሰጠህን ተቀበልለት።