Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 250 የሱስ በፍቅሩ ስለ ራራልን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሱስ በፍቅሩ ስለ ራራልን
ምኞቱ ነው በቅፉ ሊቀበለን።
ታላቁ መሐሪ እኛን ይጠራል
ልባችሁን ስጡኝ ሲል ይለምናል።
በጌታ መዳንም ከተገኘልን
ችግርን ለምን እንመርጣለን
ጸጋው ስለ ምን በከንቱ ይቀራል
ሕይወቱን ስለኛ ለውጦአል።
፪፡ በየሱስ ክርስቶስ
ዓለም ተዋጅቶአል
የኃጢአት መሥዋዕት ቀርቦአል።
ቅዱሱ ተረገመ ሊባርከን
በሞቱም ሁላችንን አዳነን
በደሙ ተደመሰሰ ዕዳችን
በደላችን ተሰርዮልናል።
ፈራጁ ስለ አጥፊዎች ተቀጣ
በልጁ ድነናል ካምላክ ቁጣ።
፫፡ በአዳም ሁላችንም እንደ ሞትን
ክርስቶስ ሁላችንን አድኖናል።
ለበደለኞች ብፅዕና ተሰጠ
የኃጢአት ዕዳ ተከፍሎአል።
ለአዳም ልጆች አርነት ተገኘ
ጽድቅና ሕይወትም የሱስ ሆነ።
ምእመናን ሁሉ በጣም ደስ ይበለን
ቸር አባታችንን እናመስግን።
፬፡ ቸሩ መድኃኒታችን ትሩፋትህ
ስለ ተሰጠን እናመስግንህ።
የኃጢአትን ወጽመድ በጥሰሃል
ከልባችን ጭንቅን አንስተሃል
የልጅነት ሥልጣን ሰጥተኸናል
ስማችን ተጻፈ በመዝገብህ
ለዘላለም እንድንወድስህ
አድርሰን ወደ ሰማይ መንግሥትህ።
