Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 249 ኢየሱስ ሲጠራህ ወደ ሰማይ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 249 ኢየሱስ ሲጠራህ ወደ ሰማይ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ኢየሱስ ሲጠራህ ወደ ሰማይ
ቸኩል ወደርሱ ሳትዘገይ።
መንገዱንም ያስተምርሃል
ፍቅሩ ይታይሃል።
ድንቅ ይሆናል ለሰማይ መናኝ
ድኖ ካምላክ ጋራ ሲገናኝ
ምን ያህል ደስታ አለው በላይ
በቤቱ በሰማይ።
፪፡ ዛሬ በቃሉ ቀርቦልሃል
ቸሩ እረኛ ፈልጎሃል።
ሰምተሃል ድምፁን ወንድሜ ሆይ
ልብህን ከፈትህ ወይ
ድንቅ ይሆናል . . .።
፫፡ ሳታመነታ ክፈትለት
ፈጥነህ ተቀበል ከርሱ ስርየት።
ዛሬ ሲሰጥህ ያምላክ ጸጋ
ልብህን አትዝጋ።
ድንቅ ይሆናል . . .።

Exit mobile version