Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 247 ለእግዚአብሔር ለሆኑት ሁሉ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 247 ለእግዚአብሔር ለሆኑት ሁሉ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ለእግዚአብሔር ለሆኑት ሁሉ
የሰንበት ዕረፍት ጸንቶላቸዋል።
የአምላክ ሕዝብ ዘላለም በብፅዕና
ከጌታ የሱስ ጋራ ይኖራል።
፪፡ አምላክ እንቦችን
ካይናቸው ያብሳል
ሞት ወይም ኀዘን አይኖርም በሰማይ።
ምድራዊ ጭንቀት ወደ ኋላ ቀረ
ዘላለም ደስታ ብቻ ነው በላይ።
፫፡ ተሰብስበው ከዓለም ክፍል ሁሉ
ጻድቃኑ ባምላክ ፊት ይቆማሉ።
የድልን አክሊል ጭነው
ነጭ ልብስ ለብሰው
ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።
፬፡ ለኔ ስትል የሞትህ ኦ ጌታ የሱስ
ከአንተ ዘንድ ዘላለም እንድገኝ
በቅዱስ እጆችህ ይዘህ እቀፈኝ
ቸሩ የሱስ የአንተ ገንዘብ ነኝ።

Exit mobile version