Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 245 የሰይጣንን መኖሪያ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሰይጣንን መኖሪያ
ስናስበው ያስፈራራል፤
የኃጢአን መሣቀያ
በጣም ያስደነግጣል፤
በዓለም እንዳንታለል
ሲኦል እንዳንገባ
የጸጋ ዘመንም ሳያልፍ
አምላክ ሆይ አነቃቃን።
፪፡ ዛፍ ተቆርጦ ከወደቀ
ተመልሶ አይነሣም፤
እንዲሁም ወደ ሰይጣን ቤት
ሰው ከገባ አይወጣም።
በሲኦል ሆኖ ስሕተቱን
ቢያምን ምን ይረባል?
የኃጢአቱን ብድራት
እንደ ሥራው ያገኛል።
፫፡ ከሞት በኋላ ንስሐ
መግባት ከቶ አይቻልም፤
አምላክ ይሰጣል ይቅርታ
ላመነው በዚህ ዓለም።
ኃጥአን ግን ካምላክ ፊት ርቀው
ሥቃይ ይቀበላሉ፤
ለዘላለም ተጨንቀው
በሲኦል ይኖራሉ።
፬፡ ሰው ሆይ፥ ፍራ ተንቀጥቀጥም
ሲኦል ተከፍቶብሃል፤
ባካሄድህ ተጠንቀቅም
ገሃነም እንዳይውጥህ።
ከዲን እሳት እንድትድን
በየሱስ የሚያምን
ልብ እንዲሰጥህ አምላክን
በጣም በትጋት ለምን።
፭፡ አምላካችን ሆይ አድነን
በቍጣህ አትቅሠፈን፤
እንደ በደላችን መጠን
መዓት አታውርድብን።
በእውነተኛ ሃይማኖት
ልባችንን አጽናልን፤
በእምነት ጸንተን ብንሞት፥
ከፍርድ እንድናለን።
