Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 244 በክርስቶስ ቍስል ውስጥ ልረፍ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 244 በክርስቶስ ቍስል ውስጥ ልረፍ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ በክርስቶስ ቍስል ውስጥ ልረፍ፥
ከአምላክ መቅሰፍት እንድተርፍ።
የክርስቶስ ሥቃይና ሞት
ይሆነኛል ሰላም፥ ሕይወት።
፪፡ ለፍርድ ስቀርብ ወዳምላክ ፊት፥
ልማጠን ነው በክርስቶስ ሞት።
ከዓለምም በሞት ስለይ፥
ልወርስ ነው ሕይወት በሰማይ።
፫፡ ሞት ሆይ የትአል ማሸነፍህ?
ልረግ ወዳምላክ በክንፍህ።
የክርስቶስ ጽድቅ ሲሆን ጽድቄ
ነፍሴን ተቀበል አምላኬ።

Exit mobile version