Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 241 የሱስ ሆይ፥ የእኔ መድኅን የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 241 የሱስ ሆይ፥ የእኔ መድኅን የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ የሱስ ሆይ፥ የእኔ መድኅን
ወደኔ ና፥ ከኔም ጋር ሁን
ከእኔ ጋር ተባበር።
በዓለም ሁሉ ፈተና
ብዙ መከራም አለና
አንተ ሰላም ሁንልኝ።
ነፍሴም ሥጋዬም በመሪር
ሥቃይ ቢቸገርም እንኳ፥
እኔን ምስኪን ተቀበልኸኝ፥
በልቤም ሰላም ሰጠኸኝ።
ኦ የሱስ ኦ መድኃኒቴ፥
መድኃኒቴ፥
አንተ ነህ መጽናናቴ።
፪፡ ምድራዊ ድንኳኔ ሲፈርስ፥
ወዳንተ ነፍሴን እንዲያደርስ፥
መልአክህን ላክልኝ።
ደካማ ሥጋ በሰላም
ይረፍ ከምድሩ ድካም
ድምፅህ እስኪያስነሣኝ።
ስነሣም ልይህ አምላክ ሆይ
ከአንተም ዘንድ አዲሱን ወይን ልጠጣ፥
በብፅዕናም ላክብርህ
ላመስግንህም መድኃኒቴ ተቀበለኝ፥
ተቀበለኝ፥
ብኖር ብሞትም ያንተ ነኝ።

Exit mobile version