Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 240 ጌታ ሆይ ጸሎቴን ስማኝ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ጌታ ሆይ ጸሎቴን ስማኝ
ዞትር አትለየኝ።
በምሄድበትም መንገድ
ፍቅህንም አውርድ።
ፍቅህንም አውርድ።
፪፡ መንፈስ ቅዱስህን ላከው
ልቤን እንዲያሞቀው።
የሰማዩን ቤቴን እንዳይ
ከዳኑት በአንድ ላይ።
ከዳኑት በአንድ ላይ።
፫፡ አምላኬ ሆይ እኔን እርዳኝ
በጣም ደካማ ነኝ።
ኃጢአቴ የከበደኝ
ጐስቋላ ምስኪን ነኝ።
ጐስቋላ ምስኪን ነኝ።
፬፡ ለመተኛት ሲመሽብኝ
ጌታ ሆይ ጠብቀኝ
ከእኔ ዘንድ አትራቀኝ
ለብርሃንህም አብቃኝ።
ለብርሃንህም አብቃኝ።
፭፡ ያንተ ናቸው ክብር ኃይልም
ዛሬና ዞትርም።
ምስጋና ለስምህ ይሁን
ለዘላለም አሜን።
ለዘላለም አሜን።