Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 24 ወደኛ ና አማኑኤል የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ወደኛ ና አማኑኤል፤
አድን ሕዝበ እስራኤልን
በስደት የሚንገላታ
እስኪገለጥ ልዑል ጌታ።
ተደሰቱ ኦ እስራኤል፥
ከኛ ጋር ነው አማኑኤል።
፪፡ ወደኛ ና የእሰይ ልጅ፤
አድነነ ከሰይጣን እጅ።
ከገሀነምም አውጣነ፤
በምትም ላይ ድል ስጠነ።
ተደሰቱ . . .።
፫፡ ወደኛ ና ቅዱስ ብርሃን፤
ኑሮአችንን አድስልን።
ጨለማን ከኛ አርቀህ፥
አቅርበን ወደ ዙፋንህ።
ተደሰቱ . . .።
፬፡ ወደኛ ና የዳዊት ልጅ፤
አሳየን የሰማይን ደጅ።
በመንገዱም አንተ ምራን፤
ከሰይጣን ወጥመድ ጠብቀን።
ተደሰቱ . . .።
