Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 237 ቀኑ መሽቶአልና የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 237 ቀኑ መሽቶአልና የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ቀኑ መሽቶአልና
ና ጌታ የሱስ ሆይ፥
በአንተ እንድጸና
ጸጋህንም ስጠኝ።
ምሕረት አድርግልኝ፤
ክብርህን ግለጥልኝ፥
ፍቅርህንም የሚገልጥ
ወንጌልን አስታውሰኝ።
፪፡ የሱስ ልቤን አሁን ሳብ፥
ወደ ቅዱስ ቃልህ።
አግባልኝ ቅዱስ አሳብ
አጥራኝ በደምህ።
ልከተልህ ደግፈኝ፥
ስፈተን ድልን ስጠኝ።
በሰማያዊ መዝገብ
እኔን በዚያ መዝግብ።
፫፡ በዚህ ዛሬ የቆየኝ
ኀዘን ሆነ ተድላ፥
ልቤን ደስ የሚያሰኝ
ወይም የሚያበሳጭ
ሁሉን ላንተ ልነግር ነኝ።
ልመናዬን ስማልኝ
መልስልኝ ኦ አባት
እንደ ጸጋህ ብዛት።
፬፡ ድኃ ምስኪንም ብሆን፥
ዞትር ላመስግንህ፤
ቀድስ ያፌን ቃል አሁን፣
እንዲሆን ለክብርህ።
እስካሁን ነህ ተስፋዬ
የዳንኩበት ጋሻዬ፥
እስካሁን የደገፍኸኝ
በየዕለቱ እርዳኝ።

Exit mobile version