Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 230 የዘላለም ምርጫዬ ነህ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የዘላለም ምርጫዬ ነህ
ወዳጄና ሕይወቴ፥
በጉዞዬ ከአንተ ጋር
ልራመድ መድኃኒቴ።
የሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር፥
የሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር፥
በጉዞዬ ከአንተ ጋር፥
ልራመድ መድኃኒቴ።
፪፡ ለዓለም ምቾትና ደስታ
ለዝናም ጸሎቴ አይሁን።
በደስታ ልሠቃይ ልሥራ፥
ብቻ ካንተ ጋር ልሁን።
የሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር፥
የሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር፥
በደስታ ልሠቃይ ልሥራ፥
ብቻ ካንተ ጋር ልሁን።
፫፡ በሞት ጥላ ውስጥ ና ምራኝ፤
ባሕሩንም አሻግረኝ።
በዘለዓለም ሕይወት ደጅ
ልግባ ጌታ ካንተ ጋር።
የሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር፥
የሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር፥
በዘለዓለም ሕይወት ደጅ
ልግባ ጌታ ካንተ ጋር።