Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 227 ቸሩ ጠባቂ ምራነ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 227 ቸሩ ጠባቂ ምራነ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ቸሩ ጠባቂ ምራነ
በሕያው ቃልህ ብርሃን።
ከመከራ ጠብቀነ
በምሕረትህ መግበን።
ቸሩ የሱስ ቸሩ የሱስ
ዘወትር ጠብቅ መንጋህን።
ቸሩ የሱስ ቸሩ የሱስ
ዘወትር ጠብቅ መንጋህን።
፪፡ ዕለት ዕለትም ጠብቀን
ብንስትም መልሰን።
እኛ የአንተ ገንዘብ ነን
ወደ ቤትህ አድርሰን።
ቸሩ የሱስ ቸሩ የሱስ
ሰማ ጸሎታችንን።
ቸሩ የሱስ ቸሩ የሱስ
ሰማ ጸሎታችንን።
፫፡ እንደ በደላችን መጠን
እኛን አትቅሠፈን።
ዳሩ ግን ጸጋህን ሰጠን
በቅዱስ ደምህ አንጻን።
ቸሩ የሱስ ቸሩ የሱስ
ወደ አንተ አቅርበን።
ቸሩ የሱስ ቸሩ የሱስ
ወደ አንተ አቅርበን።
፬፡ ወዳንተ እንመጣለን
ኃይልና ረድኤት ሁነን።
ጽኑ እምነት ፍጠርብን
ፍቅርህን ግለጥልን።
ቸሩ የሱስ ቸሩ የሱስ
ወደ ሰማይ ውሰደን።
ቸሩ የሱስ ቸሩ የሱስ
ወደ ሰማይ ውሰደን።

Exit mobile version