Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 225 የሱስ በሚመራኝ መንገድ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሱስ በሚመራኝ መንገድ
ምን ያጠራጥረኛል
እርሱ ኃይል ይሆንልኛል
ከጥፋት ያድነኛል
ሰላሙንም ይሰጠኛል
በደስታ ያኖረኛል።
ከሚመጣብኝም ሁሉ
እርሱ ይጠብቀኛል።
ከሚመጣብኝም ሁሉ
እርሱ ይጠብቀኛል።
፪፡ የሱስ በሚመራኝ መንገድ
እጅጉን ደስ ይለኛል።
ጸጋውንም ይሰጠኛል
ሕያው ምግብ ይሆነኛል።
ከድካሜ እንዲያጸናኝ
ነፍሴም እንዳትጠማ
መንፈሱ ይፈልቅልኛል
በደስታ ያጠጣኛል።
መንፈሱ ይፈልቅልኛል
በደስታ ያረካኛል።
፫፡ የሱስ የሚመራኝ መንገድ
ወደ ላይ ያደርሰኛል።
እርሱ ራሱ ተስፋዬ ነው
በደስታ ያኖረኛል።
ተስፋውን ሊፈጽምልኝ
ወደ ሕይወት ይመራኛል።
ስለዚህ እቸኩላለሁ
እንድደርስ ወደ ተስፋው።
ስለዚህ እቸኩላለሁ
እንድደርስ ወደ ተስፋው።