Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 216 የሱስ ሆይ በዚህ በምድር የዘፈን ግጥሞች
፩፡ የሱስ ሆይ በዚህ በምድር
የማርፍበት የት ላግኝ
ወደ ሰማያዊ አገር
አድርሰህ አሳርፈኝ
እመኛለሁ፥ እመኛለሁ
ካንተ ጋራ ልገናኝ።
፪፡ የምራመድበት መንገድ
እንቅፋት በዝቶበታል።
ጠላትም በብዙ ወጥመድ
ሊያጠምደኝ ይጥራል
ጐዳናዬም፥ ጐዳናዬም
በሞት ወንዝ ይወስደኛል።
፫፡ በዚህ በምፈራው ሁሉ
አንተ አደፋፍረኝ።
የተሰጠውን ላለም ሁሉ
ደምህን አሳስበኝ
ክቡር ደምህ፥ ክቡር ደምህ
ለኔ ሕይወትን ይስጠኝ።
፬፡ አንዲት ቀን እንኳን ሥጋዬን
ድል ለመንሳት አቃተኝ።
ቅዱስ መንፈስህ ሕይወቴን
መርቶ፥ ምክሩንም ይስጠኝ።
ና ኦ የሱስ፥ ና ኦ የሱስ
በድካሜ ኃይል ሁነኝ።
፭፡ ያለም ፍቅር ያለም ጥልም
ከቶ እንዳይደልለኝ።
ቢገዛልኝ ሙሉ ዓለም
ያለ አንተ ግን አይበቃኝ።
አንተ ብቻ፥ አንተ ብቻ
በውነት መንገድህ ምራኝ።
፮፡ ወደ ርኅሩኅ ልብህ ሳበኝ
በርሱ ውስጥም ሰውረኝ።
ሌላም ሁሉ ቢጠፋብኝ
ካንተ ጋራ ብፁዕ ነኝ።
ካንተ ጋራ፥ ካንተ ጋራ
የሰማይ ሰላም አለኝ።
