Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 215 እጨነቃለሁኝ በችግር ኑሮዬ የዘፈን ግጥሞች
፩፡ እጨነቃለሁኝ በችግር ኑሮዬ
ደስታህን ፍቅርህን
አፍስሰው በላዬ።
ቶሎ እርዳኝ በፍቅር
ቀኑ ሳይደርስብኝ።
ክቡር ጸጋህ በከንቱ
እንዳይቀርብኝ።
፪፡ ተስፋዬ ሙሉ ነው
በየሱስ ክርስቶስ ስም።
አይጨክንብኝም
የደከምሁ ልጁን።
የከበደ ዕዳዬን
ተሸከመው በመስቀል።
ስለዚህ እኖራለሁ
በይቅርታው ሥር።
፫፡ እንዴት እሆን ይሆን
አምላኬን ብተወው
በዓለም ጨለማ
እቸገራለሁኝ።
ወደኔ ግን ይመጣል
ብርሃን ሕይወት ሊሆነኝ
ሊወስደኝ ወደ ሰማይ
ከምድር ሥቃይ።
