Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 213 ትካዜህን ሁሉ በአምላክ ላይ ጣል የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 213 ትካዜህን ሁሉ በአምላክ ላይ ጣል የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ ትካዜህን ሁሉ በአምላክ ላይ ጣል
በእምነት ተቀበል
የርሱን ቅዱስ ቃል
በዚህ በዓለም በጣም ብትጨነቅ
የጌታን ረድኤት ከላይ ተጠባበቅ።
፪፡ ችግርህን ሁሉ ለኢየሱስ ንገር
ያዳምጥሃልና አትመረር።
ኃዘንህ ሁሉ በርሱ እስኪወገድ
አምላክን በትዕግሥት መጠበቅ ተማር።
፫፡ ብዙ የተቸገሩ ካንተ ይልቅ
እንደ አሉ ልታስብ ይገባሃል
ለነርሱም ረድኤት ልትሰጥ ብትጥር
በእርግጥ ይቀላል የራስህ ችግር።

Exit mobile version