Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982
መዝሙር 212 ስትጨነቅ ሳለህ ጥራ የሱስን የዘፈን ግጥሞች
፩፡ ስትጨነቅ ሳለህ ጥራ የሱስን
እርሱ የአንተ ረዳት ነው።
ድካምህንም ግለጥለት አሁን
ችግርህንም ንገረው።
በታላቅ ኃይሉ ሊያበረታህ ነው
ግን በራስህ ኃይል ፈጽመህ ሙተሃል።
ስለዚህ ቸኩል ወደ የሱስም ሽሽ
የጸጋ ኃይሉን ልበሰው።
፪፡ አምላካችን ጭንቅህን ሁሉ ያያል
ጩኸትህንም ይሰማል።
የሚያድስ ኃይልም ይሰድልሃል
በእምነት ብቻ ተቀበል።
አንተን ይወዳል አንተን ይረዳልም።
ነፍስህ እንድትሞት ከቶ አልወደደም
ስለዚህ የሱስን ሊሰዋ ላከው
በሞቱ አንተን አዳነ።
፫፡ ችግርህን እስኪያስወግድ ቢዘገይ
በጭንቀት ስትጐስቍል።
ወደ ላይ አሻቅበህ የሱስን እይ
ችግርህንም ያርቃል።
ተስፋህ አድርገው ለመላ ዘመንህ
እርሱ ኃይልህ ነው ከሞትም ያዳነህ።
ብርሃኑ ይሠራል በልብህ ገብቶ
እውርነትህን ያበራል።
