Site icon Treasure Hymns – Amharic

መዝሙር 21 በልደት ማታ መብራት ሲበራ የዘፈን ግጥሞች

Sibhat LeAmlak The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus vertion 1982

መዝሙር 21 በልደት ማታ መብራት ሲበራ የዘፈን ግጥሞች

 

፩፡ በልደት ማታ መብራት ሲበራ
ለክርስቲያኖች ደስታ ይሆናል።
ጥንት የተዘመረው የመላእክት መዝሙር
አሁን በድምቀት ይዘመራል።
ለአምላክ ይሁን ምስጋና
በምድርም ሰላም
ለሰውም በጎ ፈቃድ ይሁን
በአምላክ ሥምረት።
በልደት ማታ መብራት ሲበራ
ለክርስቲያኖች ደስታ ይሆናል።
፪፡ አምላክ ለምድር የሰጠው ስጦታ
ለኃጢአተኞች መድኅን ሆኖአል።
ፀሐይ በዓለም ላይ እንደሚወጣ
የሱስ ብርሃን ሆኖ መጥቶአል።
በጨለማ የሄደ ሕዝብ ብርሃንን አየ
በሞት ጥላ ለኖሩ ብርሃን ወጣላቸው።
አምላክ ለምድር የሰጠው ስጦታ
ለኃጢአተኞ መድኅን ሆኖአል።
፫፡ ደኅንነት፥ ሕይወትና ሰላም
በየሱስ ክርስቶስ ለኛ ተሰጠ።
እርሱም የወይን ግንድ ሆኖአል ለዓለም
የሕይወት ፍሬ ከርሱ ተገኘ።
ሕፃን ተወልዶልናል
ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል
አለቅነቱ በርሱ ጫንቃ ላይ ይሆናል።
ደኅንነት ሕይወትና ሰላም
በየሱስ ክርስቶስ ለኛ ተሰጠ።

Exit mobile version